የአሻራ ድራማ ገጸ ባህሪ ምስራቅ የተለያየ ስሜት በውስጣችን ፈጥራለች። በአንድ በኩል ቤተሰቧን ለመከላከል ያደረገቻቸው ነገሮችን መረዳት እንችላለን በሌላ በኩል ደግሞ ለእራሷ ደስታ ብላ ሌሎችን መጉዳቷ ትክክል አለመሆኑን እናምናለን። ግን የምስራቅን አስተሳሰብ ለመረዳት ወደኋላ ተመልሰን በህይወቷ ውስጥ እንደዚህ እንድታስብ ያደረጋት ምን እንደሆነ መረዳት እንችላለን።
ከአላዛር በፊት የተፈጠሩ የምስራቅ ገጠመኞች፦
ምስራቅ አላዛርን ከመተዋወቋ በፊት ፈታኝ ህይወት ነበራት። ገጠር ውስጥ ሴት ልጅ ሳታገባ መውለዷ የማይታሰብ ነገር ነው። ነገር ግን ምስራቅ ይሄን መምረጥ እንዳትችል መብቷን ተቀምታለች፣ በሽፍታዎች ተደፍራ ታረግዛለች። የአባቷ አንድ ሴት ልጅ ነች እናም ሽፍታው ወንድሟ ይሄን ጥቃት ያደረሱባትን ተበቅሎላታን ነገር ግን ይህ ህመምሟን ማጥፋት አልቻልም። በደረሰባት ጥቃት ሳትሸነፍ ከልጇ ጋር በአቧቷ ቤት መኖር ቀጥላለች። አካላዊ ጉዳቷ ቀስ በቀስ ቢድንም የስነልቦና ጉዳቷ ግን እንደዛ በቀላሉ የሚታለፍ አልነበረም።
ስለዚህ ያለፍቃዷ የልጅ እናት ሆና የወደፊት ህልሟን ያጨለመው ጥቃት ቀን በቀን ይከተላታል። ምንም ያለፍቃዷ የተፈጠረ ነገር ቢሆንም በገጠሩ ውስጥ ያለአባት ልጅ የምታሳድግ ሴት ከቤተሰቧ ጋር ኑሮዋን የመቀጠል ምርጫ ብቻ ነው ያላት። ህይወቷ ቢቀጥልም በማንም ያለመፈለግ ቁስል ምስራቅን ሁሌም ይከተላታል።
ህይወት ሁሌም ፈተና አይጠፋትም እና የምስራቅ ትግል እዚያ ላይ አላቆመም። ሽፍታ ወንድሟ በፖሊስ ተፈላጊነቱ ቤተሰባቸውን ሁሌም እንደረበሸው ነው። በዚህም ምክንያት ምስራቅ የምትወዳቸውን ሰዎች በማንኛውም ሰዓት ማጣት እንደምትችል ትረዳለች። ይህ በተጎዳው ስነልቦኗዋ ሌላ ሸክም ይጨምራል። ሰው አይፈልጋትም እና የሚወዷት ሰዎችን በማንኛውም ሰዓት ልትቀማ ትችላለች።
ከአላዛር ጋር የነበራት ህይወት፦
አላዛር በምስራቅ ህይወት ውስጥ የገባው ከወንድሟ ጋር የሚገናኝ አደጋ የተፈጠረ ጊዜ ነው። ስለዚህ ግንኙነታቸው የጀመረው ተረት ላይ እንደምናነበው አይነት የፍቅር ታሪክ አይደለም። ይልቅስ ምስራቅ ወንድሟ እስር ቤት እንዳይገባ አላዛርን አስታማዋለች። ነገሮች የተወሳሰቡት አላዛር ማንነቱን አለማወቁ ሲጋለጥ ነው። አላዛር ሚስት እና ቤተሰብ እንዳለው አያውቅም ነበር ስለዚህ ከምስራቅ ጋር ለመቀራረብ ምንም የሚያስቆመው ነገር የለም።
ቀስ በቀስ ሁለት ብቸኝነት የሚሰማቸው ሰዎች በፍቅር ይወድቃሉ። ሌላ ልጅ ይወልዳሉ እና አላዛር ለምስራቅ ቤተሰብ እና መንደር ምርጥ ሰው ነበር፣ ህይወታቸው ፍጹም ሆኖ ይቀጥላል። ግን አላዛርን ማፈላለግ ያላቆመ ወንድሙ ነበረው ስለዚህ ወሬው የምስራቅ ሰፈር መድረሱ አልቀረም። ግን እውነቱን ስታውቅ ምስራቅ አላዛርን ስለሚጠብቀው ቤተሰብ ሳይሆን፣ አብረው ስለመሰረቱት ቤተሰብ ነበር። ያን ሁሉ አመት ብቻዋን እንደምትቀር ስታምን ቆይታ በመጨረሻ ፍጹም ፍቅር አግኝታለች። ስለዚህ እንዴት ደግማ ልትቀማ ትችላለች?
የምስራቅ ፍራቻን ማንኛችንም ልንረዳው የምንችለው ነገር ነው። ግን ፍርሀት ትክክለኛውን ምርጫ ከመምረጥ ሲጋርደን የምንወዳቸውን ሰዎች መጉዳት እንጀምራለን። ከእዛ ጊዜ በኋላ የወሰነችው ውሳኔ ቤተሰቧን እየጎዳ እና ከአላዛር እያራራቃት ነው የሄደው። ዞሮ ዞሮ የፈራችውን ነገር እንድትጋፈጥ ተገዳለች።
ምስራቅ ምንም ያህል ለሌላ ሰው እራስ ወዳድ የሚመስሉ ውሳኔዎችን ብትወስንም፣ ምርጫዎቿ ያደረሱትን ጉዳቶች ማገናዘብ ችላለች። የአላዛርን የመጀመሪያ ቤተሰብ ስትተዋወቅ፣ ልጁ ቤርሳቤህ እና ወንድሙ ዮናስ አላዛርን በማጣቸው እንደተጎዱ ተረድታለች። እናም ይሄ እውነት ሲቀርብላት እንዴት በእነዚህ ሰዎችን ህመም ላይ ውሳኔዋ እንደጨመረ ትረዳለች። የምስራቅ እድገት ከዚህ ይጀምራል። ቤርሳቤህን እና አባብልን ይቅርታ ጠይቃ፣ አላዛር ለማስታወስ የሚያደርገውን ህክምና እንዲቀጥል ተመልሳ ወደ ቤቷ ትመለሳለች።
አሻራ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል ይቀርባል!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed