የሞያ ልክ ከገበታ ሜዳው የባል ታማኝነት የአብሮነትና የእናት እጅ የሚፈተንበት የፍቅር እና የእጅ ውጤት ዳኝነት እስከ መጨረሻው ይታይበታል በሁለቱ ጓዳ ።
እውነተኛ ፍርድ የምድር ከባዱ አጋጣሚ ነው እያወቁ ለአንድ ወገን መፍረድ በምርጫ ደሞ አንዱ ማስቀደም ሌላው የወንድ ልጅ ፈተና ከውሳኔው በኋላ እንዴት እኔን መለየት ከበደው ያሳደገው እጅን መረሳት የሚለው የእናት ቅሬታ ድህረ ምርጫ ቅራኔው ነው እንዲሁም ከምርጫ በኋላ የሚስት ትኩሳት የፍቅሬን ልክ የሞያ ጣዕሜን መለያ ከበደህን በሚል ወንድ ልጅ የምርጫ ፀፀት ደስ የሚል ስቃይ ይገጥመዋል በሁለት ጓዳ ።
እንዳው በህይወት ብዙ ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች እንዳሉ እሙን ነው ቅድሚያ የሚሰጠው ጭምር እናት እና ሚስትን በተመለከተ ወንድ ልጅ እርሶ ምን ይሆን የውሳኔ ምርጯዎ ።
እነሆ መሰረታችን ሁለት ጓዳ ነው የእናት እና የሚስትን ሞያ እንደ መምረጥ ሁሉ በሁኔታዎች ውስጥ ማንን ወንድ ልጅ ያስቀድማል እናት ወይስ ሚስትን እንመልከት ።