ግዛቸው አንድ እና አንድ እቅድ ነበረው። አዲና እራሷን ማጥፋት እስክትፈልግ ድረስ ተስፋ ማስቆረጥ። ባለፉት ክፍሎች በተፈጠሩት ክስተቶች ምክንያት እቅዱን እንዳሳካ ያምናል። ግን አዲና ግዛቸው ቅስሟን እንዲሰብረው አልፈቀደችም፣ ትክክለኛውን ማንነት አውቃ ለመፋለም ዝግጁ ነች።
ግዛቸው አዲናን ለመበቀል የተለያዩ እቅዶችን አካሂዷል።
- እቅድ 1፡ ከቤተሰቧ አለያይቶ አዲስ አበባ ውስጥ ብቸኛ ማድረግ
አዲና ከስሜነህ ጋር አዲስ አበባ ስትመጣ እቅዱ ተበላሽቶበት ነበር። ይሄን ነገር ስሜነህን በተለያየ መንገድ ወደ ዳር መልሶታል። ከዚህ በኋላ አዲና ብቻዋን ቀረች? አልቀረችም! ይልቅስ ወዲያው ከጥሩ ሰዎች ጋር በመቀራረቧ መቼም ብቸኛ እንዳትሆን አድርጓታል።
ስለዚህ የግዛቸው እቅድ አልተሳካም።
- እቅድ 2፡ አዲናን በቅርብ ሆኖ ለማሰቃየት የሚያሳምን አዲስ ማንነት መፍጠር
አዲና አዲስ አበባ እንደገባች ለሚያጋጥሟትን ችግሮች የሚደርስላት ታማኝ ነው ብላ ያሰበችው ሰው፣ ንጉሱ ብሎ እራሱን ያስተዋውቃል። ግዛቸው ንጉሱ የሚለውን ስም የመረጠው በአዲና ህይወት ላይ ኃይል ያለው እሱ ብቻ መሆኑን ለማሳወቅ ነው። ንጉሱ የአዲናን ጭንቀቶች “በመፍታት” እንድታምነው አድርጓታል።
ስለዚህ የግዛቸው እቅድ ተሳክቷል።
- እቅድ 3፡ አዲናን ከባልንጀራዎቿ ጋር ማጣላት
ግዛቸው ስሜነህን ምንም ያህል ከአዲና ሊያርቀው ቢሞክርም፣ ምንም ሊሳካለት አልቻለም። ስለዚህ ምትኬ ለስሜነህ ያላትን ፍቅር ሲደርስበት እቅዱን የሚያሳካ መፍትሄ ያገኛል። ምትኬ እና ስሜነህን በጣም የሚያሰክር እጽ አጠጥቶ አብረው እንዳደሩ ያስመስላል እናም አዲና ይሄን ስታይ የምትወዳቸው ሁለት ሰዎች እንደበደሏት ታምናለች።
ስለዚህ የግዛቸው እቅድ ተሳክቷል።
- እቅድ 4፡ የአዲናን ቤተሰብ ገድሎ እንድታገባው ማሳመን
የግዛቸው የመጨረሻ እቅድ አዲናን ከእሱ በስተቀር የምትተማመንበት ማንም ሰው እንዳይኖር አድርጎ በእጁ ስትገባ ቅስሟን መስበር ነበር። ነገር ግን ቤተሰቧ ቤታቸውን ካነደደው እሳት አምልጠው አብረዋት መኖር ይጀምራሉ። ይሄንን ባለማሳካቱ ተበሳጭቶ፣ ሊያገባት የቤተሰቧን ፍቃድ ያገኛል። እናም ትልቁ በቀሉ በጣም የምታምነው ሰው በሰርጓ ቀን ላይ ሲበድላት ቅስሟ እንዲሰበር ነው።
የመጨረሻውን የእሳት እራት ክፍል ዛሬ ማታ 2:30 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed