channel logo
Dinknesh S1

ከወርቅ ይልቅ ውብአለም ተፈትናለች !

ዜና
02 ኤፕሪል 2025
የምድር ህይወት የኑሮ እጣ ፋንታ።
Dinknesh

የምድር ህይወት የኑሮ እጣ ፋንታ በፍላጎት አይደለም የሚመራው ይባላል ሰውም ቢሆን በተፈጥሮ ህግ በነብስ ጥሪ እንጂ በሚለው የሃሳብ መነሻ ላይ ብዙ ሰዎች ይስማማሉ ። 

የውብአለም ህይወት ደሞ እውነትም የሰው ልጅ በነብስ ጥሪ ነው እንጂ በፍላጎት አይኖርም ለሚለው የሃሳብ አፅናፍ ያደላ ይመስላል በአንድ ወቅት የአዘቅት ቁልቁለት ኑሮ ትኖር የነበረችው ውብአለም የትምህርት ፣ የኑሮ የአስተዳደግ የፍቅር ጉድለት የነበረባት የዛሬዋ ባለ ወርቃማ ስኬት ባለቤት ብርቱ እንሰት ውባአለም የልጅነት አስተዳደግ የትምህርት ደረጃዋ ለዛሬው ማንነት ያለው ድርሻ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። 

ተብሎ የሚታለፍ ነወ ማለት አይቻልም ይልቁንም ምንም ድርሻ የለውም ያቺ መፍጠሯ በራሱ እርግማን የሆነባት ፣ ያቺ በወላጅ እናቷ ሳይቀር የሚታፈርባት ፣ ያቺ የትምህርት ነገር የማይዘልቃላት በእድሜ አቻዋ ሁሉ የሚሾፍባት እስክ አምስተኛ ክፍለ እንኳን በአግባቡ መዝለቅ ያልቻለችው ውብአለም ተፈጥሮ በሰጠቻት ክህሎት ሀገርን በአንድ ድምፅ አንደኛ የሚያስብል ድንቅ የመድረክ ተዋናይ ሆና ሀገር ይዛለች ። 

ይቺ ልክ እንደ ድመት ክፍ ክፍ ተብላ ያደገችው ውብአለም በእድሜ እኩያ የተናቀች ተስፋ አልባ ልጅ የነበረችው ብርቱ እንስት በመድረክ ስራ ለታሪክ የሚቀመጥ በልጅ ልጅ የሚነገርለት የትወና ብቃት ይዛ በትንሽ አጋጣሚ የመድረክ ንግስት የመሆኗን የክስተት ኩነት ብዙ ጠላት ይዞ መቷል ። 

የእሷ ባላንጣዎች የልጅነት ጥቁር የሚባል ታሪኳን እየመነዘሩ የትምህርት ፣ የልጅነት አስተዳደግ ፣ የቤተሰብ ሁኔታዎችን እያነሱ ለማሸማቀቅ በሴራ የተሞላ የተናበበ ዘመቻ ጀምሮአል ውበአለም በልጅነቷ ሰው ቤት ትሰራ ነበርና ፣ በእናቷ ወዳጅ መደፈሯን እየመነዘሩ ይቺን ብርቱ እንስት ድሮ የምትሰራበት ቤት ልጅ የእኛ ቤት ሰራተኛ ነበረች ይቺ ምናምንቴ እያለች የመድረክ ተፎካካሪ የስራ ውድድር ላይ መገናኘት በብቃት መጓዝ ከባድ ሲሆንባት የስም ማጥፋት ዘመቻ ይዛለች ፣ ውባአለም ግን የምትረታ የዋዛ ሰው አይደለችም በፅናት ቆማለች ። 

ከእናቷ ጋር ሆና ብዙ መከራ ያየችው ውብአለም ህይወት ያለ ጥናት ፣ ትምህርት የፈተነቻት ብረት ናት ከወርቅ በላቀ የችግር እሳት የተፈተነች ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ በሃሰተኛ የአምስተኛ ከፍል ትምህርት ማስረጃ በተቀጠረችበት ትያትር ቤት ውስጥ የመድረክ ንግስት ሆናለች ይህ ነገር ያልተዋጠላቸው አያሌ የሚባሉ ሰዎች ብዙ ሙከራ ላይ ናቸው ይሆን ሆይ ውብአለም መልስ አላት ። 

በውብአለም ታሪክ ላይ አስተማሪ የሚባሉ የብዙሃን ገፆች አሉ ግን ይህን ከባድ ችግር የሚያልፉ ሰዎች ልዩ ይባላሉ ውብአለም የፊት እንጂ የኋላ ታሪክ የላትም የስኬት ማለት የፊቷ የሚያሳሳ በእሾህ የተሞላ ሊሆን ተቃርቧል የሚሉትን በብቃት ዘርራ የፊት ለመሆን በሂደት ላይ ናት ውብአለም ከወርቅ በላይ የተፈተነች ብርቱ እንስት ።

#ድንቅነሽ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv
Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed