channel logo
Dinknesh S1

ውብአለም የአይበገሬነት ተምሳሌት።

ዜና
27 ኤፕሪል 2025
እንደወርቅ ተፈትኖ የደመቀው የውብአለም ሂወት።
Dinknesh

ድንቅነሽ ድራማ ፣ የመርገፍ ህይወት ለዳግም ማበብ መሰረት መሆኑ የታየበት ድንቅ ጉዞ ስንብት ሲታወስ ..... 

ሰው ለክብር ፣ ለድል ለመሪነት የታጨ በመሆኑ ፅልመት ችግር የሚገጥመው በስንክሳር የተወጠረ ምሳሌ አለት ነው ፣ ህይወትም ቢሆን በጥረት የተሞላች የመንፈስ ጠንካሮች ብቻ የሆነች አሸናፊ የምታነግስ የፊተኞች መድረክ ናት ድንቅነሽ ድራማ ይህን የህይወት ያልተፃፈ ህግ በሚገርም የመቼት ውህደት ፣ የሃሳብ ግጭት የአቅጣጫ ለውጥ እየሰነደ አስገራሚ የእድል እና የህይወት ግጥምጥሞሽን በጥሩ የምስል ቅንብር የቃላት ስደራ የታሪክ ፍሰት የተዋበው ድንቅነሽ ድራማ በውብአለም የህይወት ምህዋር ከትቢያ መነሳት የመድረክ ንግስት የመሆን ተአምራዊ የህይወት ገፅ አንድ ፣ ሁለት ፣ ክስተታዊ መቼት ለየት ያለ ። 

ድንቅነሽ ድራማ ዋጋ አልባ የተባለችውን ውብአለምን የመድረክ ፈርጦች የዋሉበትን መድረክ የምታፀዳ በኑሮ የተዳከመች ሴት የምታፀዳው የቲያትር መድረክ ላይ ደምቃ ብቅ ማለቷ እንዲሁም በእነ ርብቃ በኩል የተወደደ ባህሪ መሆን አልቻለም ምክንያቱም ውብአለም የነ ርብቃ የቤት ውስጥ አገልጋይ ነበረች እንዲሁም ህይወት ክፉኛ ደቁሳት ግራ መጋባት ውስጥ ሳለች በዛውም ላይ ልጅ ይዛ የሰቀቀን ህይወት ስትገፋ የነበረችው የበታች የተባለችው ሴት የተመፃዳቂ ርብቃ ተቀናቃኝ ሆና የፊት የማትቀመስ የመድረክ ተዋናይ ህዝብ በአንድ ልብ የሚዘክራት ባለሞያ የመሆን ጉዳይ ለርብቃ ምላጭ መዋጥ ያክል ነው ። 

ይህን መገፋፋት በሚገርም ቅንብር ጉድ እንዴ እያስባለ የሚዘልቀው ድንቅነሽ ድራማ የህይወት ጥሪ የማትሸሽ የትም ይሁን የት መደበቂያ የላትም የሚለውን ነገር ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የርብቃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመታየት የምታደርገው ጥረት በቅናት የተሞላ መሆኑ ዋጋ እንደሚያስከፍል የሚያሳይ እና የውብአለም የቅፅበት የመድረክ ላይ ትወና የዘላለም ስኬት መንገድ ጠራጊ ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ተከስቷል በዚህ የህይወት የእውነት አለም መስታወት በሆነው ድራማ ውስጥ በፈርጅ በፈርጅ የተቀነባበረ ግጥምጥሞሽ ውስጥ ሁሉም አይነት ተንኮል ፣ ምቀኝነት መጠላለፍ ፣ የአጋጣሚ ሃይል በግልፅ በሚልይበት ሂደት ውስጥ ውብአለም አምላክ ኑሪበት በዚህም አመስግኚ ሲላት ከእሳት የበለጠ ሞያን አደላት ። 

የአጋጣሚ የመድረክ ልምምድ ደሞ መፍካት ሆነላት እሷም ቢሆን በቀናው መንገድ የምትጓዝ በመሆኗም ጭምር ውጤታማ ሆነች ይህም ጉዞ የሰው ልጅ እጣፈንታ የሚባል ክስተት ነው ያስብላል የውብአለም ታሪክ በድንቅነሽ ድራማ ውስጥ ። 

በእሾህ አሜከላ የተከበበው የውበአለም የስኬት ጉዞ የመድረክ ላይ ንግስታዊ ህይወት የተሰጥኦ እንጂ የፍላጎት አይደለም ሆኖም ግን በመድረክ አዘጋጆች የሞያ ይከበር ብርቱ እንቅስቃሴ ምክንያት ከፍ ያለችው ውብአለም የሚወረወረውን ድንጋይ እየለቀመች ቤት ገንብታ ወሬውን ለባለ ወሬኛው በመተው የሀገሪቱ የመድረክ ፈርጥ መሆን ቻለችበት ድንቅነሽ ድራማ የህይወት አሸናፊ ባለ ድሎችን የሚዘክር የውጣ ውረድ ገፅን አመልካች የድንቆች ትዕይንት የእውነት ፍልሚያ ሜዳ ሆኖ የዘለቀ መርገፍ ለዳግም ማበብ የሆነላቸው ምርጥ ምርጦችን መነሻ ሲያሳይ የከረመ እንዲሁም ክፋት የመንገድ ላይ እሾህ ሆኖ አድራጊዎቹን ሲያሰናክል የሚያሳይ ፣ ሞያ ዋጋ እንዳለው የሚያትት የተፈጥሮ ስጦታ ደሞ ማርሽ ቀያሪ የስኬት አፋጣኝ አንዱ ማቀጣጠያ መሆኑን በገሃድ አመላክቷል ይህ ሰዋዊ ድራማ በዚህ መነሻ ሃሳብ ላይ ሆኖ ብዙ አመራምሮ እነሆ ግብአት ሊለን ትዝታ ጥሎ ለማለፍ ከበር የቆመ እንግዳ ምሳሌ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ። 

በድንቅነሽ ድራማ ውስጥ ስራ ፣ ለመኖር መትጋት ሳይሆን ለታሪክ በነገ ትውልድ ለመዘከር መስራት ለዛሬ ስኬት የህይወት ሙላት ዋስትና መሆኑን  በሁሉም የድራማው ከፍል ውስጥ አሳይቷል የርብቃ የተደራጀ ሴራ የስም ማጥፋት ዘመቻ የጥላቻ ድምፅ ሆኖ ጆሮ ያጣበት አጋጣሚ የድራማው አንዱ ክፍለ ሲሆን ከምንም በመነሳት ታላቅ መሆን እንደሚቻልም ያሳየ ከትልቅ መፈጠር ሳይሆን ለትልቅ ተግባር እራስን ማጨት ዋጋው ከፍተኛ ሚዛኑ የሚደፋ መሆኑን ያሳየ ጥሩ ድራማ ጭምር ነው ። 

ድንቅነሽ ድራማ የፊት ገፅ መልኮች በልፋት ድካም የሚመጡ የስኬት ዋንጫ መሆናቸውን የሚያሳይ ትልቅ ድራማ ነው የውብአለም የጀብዱ ህይወት የርብቃ መቸኮል የስኬት አዳኝ ሆኖ ለመገኘት የምታደርገውን ፍጋት የሚያሳይ መመልከት እንጂ መተረኩ የማይመጥነው የልብም ፣ የተግባርም መድረክ ነው ድንቅነሽ ድራማ ።

#ድንቅነሽ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv
Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed