ተሰጥኦ ከፍላጎት ይበልጣል ፣ ከህይወት ጥሪ ግን አይበልጥም የድንቅነሽ ድራማ አስኳል ሃሳብ ይሆን ።
የብዙዎች ህይወት ፣ የስኬት ጅማሮ መነሻው ዜሮ ምንም ነው በሂደት ግን እድል በመጠቀም በለውጥ ሃሳብ ውስጥ ሆነው የፊት በመሆን የእድል ተጠቃሚ የደረጃ ባለቤት አንድኛ ሆነው ምሳሌ ታሪክ የሚሆኑት እነሱ ይሆናሉ ድንቅነሽ ድራማም ቢሆን የልፋት መንገድ ከባድ ቢሆንም ማለፊያው ትጋት መሆኑን አሳይቷል እርሶስ ከዚህ ድራማ ምን ተማሩ ? የድንቅነሽ ጌጥ የድራማው የታሪክ ባለቤት ውብአለም ውጣ ውረዷ በአጀብ የተሞላ በተንኮል የተከበበ ነው ሆኖም ግን ውብአለም ይህን ሁሉ በፅናት ቆማ የበረታች መፅናት አስከባሪ መሆኑን ህያው አስተማሪ ናት ።
ድንቅነሽ ድራማ ዋጋ አልባ የተባለችውን ውብአለምን የመድረክ ፈርጦች የዋሉበትን መድረክ የምታፀዳ በኑሮ የተዳከመች ሴት የምታፀዳው የቲያትር መድረክ ላይ ደምቃ ብቅ ማለቷ እንዲሁም በእነ ርብቃ በኩል የተወደደ ባህሪ መሆን አልቻለም ምክንያቱም ውብአለም የተቀናቃኟ የቤት ውስጥ አገልጋይ ነበረች እንዲሁም ህይወት ክፉኛ ደቁሳት ግራ መጋባት ውስጥ ሳለች በዛውም ላይ ልጅ ይዛ የሰቀቀን ህይወት ስትገፋ የነበረችው የበታች የተባለችው ሴት የተመፃዳቂ ርብቃ ተቀናቃኝ ሆና የፊት የማትቀመስ የመድረክ ተዋናይ ህዝብ በአንድ ልብ የሚዘክራት ባለሞያ የመሆን ጉዳይ ለርብቃ ምላጭ መዋጥ ያክል ነው ።
ድንቅነሽ ያለፈ ህይወት ለሚጎትተን ለህይወት ለውጥ ድሮ የሚገደን ሰዎች የሰው ልጅ ከትልቅ መወለዱ ሳይሆን እራሱን ለትልቅ ሹመት ማጨቱ ትልቅ ያስብለዋል እንጂ ሀረጉ ዋጋ አልባ ነው የሚለውን ሃሳብ በጥሩ የምስል ክስተት የድርጊት ውጤት የልፋት ውጤት ያመጣ ሰው መክበሩ አይቀሬ መሆኑን ድንቅነሽ አሳይቷል ከዚህ አንፃር ይህን ድንቅ ድራማ ምን ነግሮን ይሆን ?
የህይወት መገፋፋትን በሚገርም ቅንብር ጉድ እንዴ እያስባለ የሚዘልቀው ድንቅነሽ ድራማ የህይወት ጥሪ የማትሸሽ የትም ይሁን የት መደበቂያ የላትም የሚለውን ነገር ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የርብቃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመታየት የምታደርገው ጥረት በቅናት የተሞላ መሆኑ ዋጋ እንደሚያስከፍል የሚያሳይ እና የውብአለም የቅፅበት የመድረክ ላይ ትወና የዘላለም ስኬት መንገድ ጠራጊ ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ተከስቷል በዚህ የህይወት የእውነት አለም መስታወት በሆነው ድራማ ውስጥ በፈርጅ በፈርጅ የተቀነባበረ ግጥምጥሞሽ ውስጥ ሁሉም አይነት ተንኮል ፣ ምቀኝነት መጠላለፍ ፣ የአጋጣሚ ሃይል በግልፅ በሚልይበት ሂደት ውስጥ ውብአለም አምላክ ኑሪበት በዚህም አመስግኚ ሲላት ከእሳት የበለጠ ሞያን አደላት በዚህ ሂደት ውስጥ ሰው ከብሮ ይታያል የዛሬ የኛ ህይወት ምን ይሆን ።
የአጋጣሚ የመድረክ ልምምድ ደሞ መፍካት ሆነላት እሷም ቢሆን በቀናው መንገድ የምትጓዝ በመሆኗም ጭምር ውጤታማ ሆነች ይህም ጉዞ የሰው ልጅ እጣፈንታ የሚባል ክስተት ነው ያስብላል የውብአለም ታሪክ በድንቅነሽ ድራማ ውስጥ ።
በእሾህ አሜከላ የተከበበው የውበአለም የስኬት ጉዞ የመድረክ ላይ ንግስታዊ ህይወት የተሰጥኦ እንጂ የፍላጎት አይደለም ሆኖም ግን በመድረክ አዘጋጆች የሞያ ይከበር ብርቱ እንቅስቃሴ ምክንያት ከፍ ያለችው ውብአለም የሚወረወረውን ድንጋይ እየለቀመች ቤት ገንብታ ወሬውን ለባለ ወሬኛው በመተው የሀገሪቱ የመድረክ ፈርጥ መሆን ቻለችበት ድንቅነሽ ድራማ የህይወት አሸናፊ ባለ ድሎችን የሚዘክር የውጣ ውረድ ገፅን አመልካች የድንቆች ትዕይንት የእውነት ፍልሚያ ሜዳ ሆኖ የዘለቀ መርገፍ ለዳግም ማበብ የሆነላቸው ምርጥ ምርጦችን መነሻ ሲያሳይ የከረመ እንዲሁም ክፋት የመንገድ ላይ እሾህ ሆኖ አድራጊዎቹን ሲያሰናክል የሚያሳይ ፣ ሞያ ዋጋ እንዳለው የሚያትት የተፈጥሮ ስጦታ ደሞ ማርሽ ቀያሪ የስኬት አፋጣኝ አንዱ ማቀጣጠያ መሆኑን በገሃድ አመላክቷል ይህ ሰዋዊ ድራማ በዚህ መነሻ ሃሳብ ላይ ሆኖ ብዙ አመራምሮ እነሆ ግብአት ሆኖ ትዝታ ጥሎ አልፎአል ።
ድንቅነሽ ድራማ የሞያ ትጋት ፣ የፍቅር ጥግ ፣ ለክብር የሚደረግ ፍልሚያን የሚያሳይ ባለሞገስ አስተማሪ ድራማ ነው በሃሳብ የነገሰ መስራት ያስከብራል የሚለውን በእውነት ያሳየ ሃይል የተሞላ ድንቅ ትዝታ የሆነ ድራማ ነው ድንቅነሽ ድራማ ።
#ድንቅነሽ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv
Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed