channel logo
Marefiya S1
channel logo

Marefiya

465ComedyPG13

የአቦል ቲቪ አዲሱ ኮሜዲ “ማረፊያ” ን ገጸ ባህሪያት እንተዋወቃቸው

ዜና
15 ሜይ 2025
ማረፍያ ሰራዊት ፍቅሬ፣ አሸናፊ ማህሌት እና አቤል ሰለሞን የመሳሰሉትን ዝነኛ ተዋንያት ይዞ በአቦል ቲቪ ቀርቧል።
Marefiya S1 article 1

ጥርስ የማያስከድነው ምርጥ ኮሜዲው ማረፍያ ከጀመረ ሁለት ሳምንት ሆኖታል። ረቡዕ ማታን በጉጉት እንድንጠብቅ ያደረገን ድራማ  በአቶ አዲሱ መኖሪያ ቤት ጊቢ ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን፣ አቶ አዲሱ አንድ በማደጎ ያሳደጓት ሴት ልጅ ከእንግሊዝ አገር የምትመጣ፣ ከሃዋሳ አካባቢ የመጣች ሰራተኛ፣ ሶስት ከተለያዩ ቦታ የመጡ አዋተው ባንድ ቤት ውስት የሚኖሩ ወጣት ወንድ ቤት ተከራዬች እና እዛ አካባቢ የምትኖር ሴት ወጣት የጎዳና ተዳዳሪ የነበረች እራሷን አሻሽላ የታክሲ ሹፌር የሆነች ነው፡፡

አቶ አዲሱ [ኮሎኔል]

በስልሳዎቹ አጋማሽ የሚገኙ፣ በአየር ሃይል እና በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት በሃገር ውስጥ እና በውጭ አገር በመስራት አገራቸውን ህዝባቸውን በቅንነት ያገለገሉ እና በዚህ ሰአት በጡረታ የተገለሉ ናቸው፡፡ሰው የሚወዱ በተለይ ወጣት የሚወዱ ወጣትም የሚወዳቸው አራዳ የሚባሉ አይነት አዛውንት ናቸው፡፡ ለሰይፈ፣ ዳኒ እና ብሩክ ሌላ ሰው እድል የሰጧቸው እንደ አባት የሚንከባከቡ አከራይ ናቸው።

ሰልፊ

የቤት ሰራተኛ ወሬ የምትወድ፣ ወደቀ ሲሏት ተሰበረ አደለም ሞተ የምትል የዋህ ሰው በልቶ የጠገበ የማይመስላት የአቶ አዲሱ ሰራተኛ ነች። በወሬ ወዳድነቷ ለህግና ለስረአት ደንታ የሌላት መሆኗ እና በሙያዋ ብዙን ጊዜ ከአቶ አዲሱ ጋር በአብዛኛው ጊዜ ትጣላለች። አሰለፈች የተባለ ስሟን ሰልፊ ብላ አቆላምጣ በግድ ሰልፊ በሉኝ የምትል አዝናኝ ገጸ ባህሪ ነች።

ሰይፈ

የሀረር  አካባቢ ልጅ ሲሆን አዲስ አበባ ፍቅረኛውን ተከትሎ መጥቶ በመንግስት መስሪያ ቤት ቅጥር ጥበብን የሚወድ እውነት ተናጋሪ ወንድ ነው። በአዲስ አበባ ህዝብ አኗኗር የሚገርመው፣ “ሰው እዴት በሩን ዘግቶ ይኖራል?” ብሎ የሚታዘብ።

ዳኒ

ዳንኤል ሰነፍ የማይዘጋጅ እንቶ ፈንቶ የሆኑ ፕሮግራሞችን በመስራት የሚታወቅ ጋዜጠኛ ነው፡፡  በጣም አፍቃሪ በፍቅር የሚያምን ፍቅረኛው ያለችውን የሚሰማ፡፡ የፍቅር ጥቅስ የሚያበዛ  ግጥም መፃፍ የሚወድ ግን የማይችል ነው።

ብሩክ

ዘፋኝ መሆን የሚፈልግ ግን ድምፅ የሚባል ነገር የሌለው በገገማ። ክለብ የሚሰራ ወቅቱ ያመጣውን የሶሻል ሚዲያ ሃሳብ በማንሳት የኪነጥበብ ስራ ሰርቶ ባቋራጭ እውቅናና ገንዘብ ለማግኘት የሚጣጣር በጣም ታዋቂ ለመሆን ጉት ያለው።

እድላዊት

አቶ አዲሱ ያሳደጓት እጅግ ዘመናዊ፣ ዘመኑ ያፈራቸውን ቲክኖሎጂዎች ሁሉ የምትጠቀም  ፋሽኖችን የምትከተል ቀበጥ ግን ደግ ጎበዝ እና ኮንፊደንስ ያላት እንደ አባቷ በማንበብ የምታምን ግን ፋሽን እና ቴክኖሎጂ የሚያሸንፋት፡፡

ቹቻ

ጎዳና ላይ ተወልዳ ያደገች ግን በራሷ ጥረት መንጃ ፍቃድ አውጥታ የታክሲ ሹፌር የሆነች በጣም የአራዳ ልጅ። በስራ የምታምን እራስሷን ለመለጥ ዘግይታም ቢሆን ትምርት የጀመረች።

ማረፍያ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed