abol tv logo

የመዝናኛ እልፍኙ አቦል ቲቪ።

ዜና
20 ሜይ 2025
በአማራጭ የተሞላው ተወዳጁ አቦል ቲቪ።
Abol TV

በአማራጭ የተሞላው ተወዳጁ አቦል ቲቪ  የመዝናኛ እልፍኙ እልፍ ነው እርስዎ ምርጫዎ የቱ ይሆን ፣ ማረፊያ ፣ ደማቆቹ ፣ ግዛት ፣ የቤት ጓዳ .......... የቱ ይሆን ..... 

በአማራጭ የተሞላው አቦል ቲቪ ሁሉም አለው ከልጅ እስከ አዋቂ የሚዝናኑበት ፣ ቁምነገር የሚያዝበት ህይወት ቀያሪ ሃሳብ የሚገኝበት ስብዕና የሚገራበት አዝናኝ ፣ ሀሴት የሚሰጡ ድራማዎችን ፣ ሴትኮሞችን በፈርጅ አድርጎ እንደ ምርጫዎ ይዞ ቀርቧል የመዝናኛ እና የቁምነገር አምድ በሆነው አቦል ቲቪ ላይ ማረፊያ አረፍ ብለን የምናየው የብዙዎች መልክ ሆኖ በሳቢነት  ከአንጋፋዎቹ አርቲስቶች እስከ ወጣት ተዋንያን የሚሳተፉበት የባህሪ ልዩነት የትውልድ አስተሳሰብ በግላጭ የሚታይበት  ማረፊያ የስራ ፣ የገንዘብ ፣ የእውቀት የስብእና ልዩነት በጥምረት ሆነው በእውን የሚሸመንበት ሳቅን ከቁምነገር አጣምሮ በይዘቱ በልፅጎ በሳምንት ሁለቴ በተወዳጁ አቦል ቲቪ በስንዱ ይጠብቆታል ።


እንዲሁም የሃሳብ ነፃነት የእንግዶች ከፍታ ፣ ሰውነት የሚታይበት ደማቆቹ  በጉጉት የሚዘልቅ ያለፈውን የማይረሳ መጪውን መሰረት የሚያደርግ የዝነኞች ሜዳ የህይወት አካፋይ አንዱ መልክ ነው በአማራጭ የቀረበ ነው ። 

ደማቆቹ መሰናዶ ውስጥ አዋቂ የእንግዶች ባህሪን የተረዳ በዛው ባህሪ ላይ ተንተርሶ አዝናኝ ሳቅ ጨዋታ ጫሪ ጥያቄዎችን በማቅረብ እንግዶችን በማዝናናት የሚወዱትን ቀድሞው የተረዳ በመሆኑ ተመልካች እና እንግዳው ለሰውነት በቀረበው ጥያቄ በእኩል ተዝናኖት በደማቆቹ ይደምቃል ። 

መቼም ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል ይሉ የሀገሬ አበው በዚህ አሳታፊ ፣ አሸናፊነት በጋራ መስማማት ማለትም ተሸናፊው አምኖ እና ፈቅዶ እንካ ድሉን በሚልበት መሰናዶ ላይ በአቅራቢው የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች ለእንግዳው ቤተኛ ናቸው እሱም በደስታ ያለ ማፈርና ወደኋላ ማለት ሁሉንም ጥያቄ አዝናኝ በሆነ መልኩ ይመልሳል ማቆቹ በዚህ መልኩ የቤተሰብ ጨዋታ መስሎ ይዘልቃል በአቦል ቲቪ በአማራጭ ያለ ነው ። 

ሌላው የአቦል ቲቪ የማይታለፍ የመዝናኛ ፣ አምድ የእርሶ ምርጫ ግዛት ነው ይህ ድራማ የህይወት ቅፅበት የደቂቀ ስህተት ግዙፍ ችግር ይዞ የሚከሰት መሆኑን የሚተርክ የቤተሰብ ዋና ፣ የትዳር ህይወት የእምነት ዋጋው ፣ የልጅ ፍቅር የንግድ ሹኩቻ የክብር ነገር በሃረግ በፈርጁ  ታጅበው የሰው ልጅ የማስመሰል ጥግ የሚታይበት የወንጀል ፣ የፍቅር ፣ የንግድ ምስጥር ለቤተሰብ ፍቅር እና ክብር መስዋዕትነት ተሸርቦ በድንቅ ትዕይንት በአስገራሚ ትወና በአማራጭ ቀርቧል በተወዳጁ አቦል ቲቪ በግዛት ድራማ ውስጥ የክፋት ጥግ ፣ የማስመሰል ልክ ፣ የትብብር እና የሴራ ህብረት ለጥቅም ሲባል ብቻ እንዴት እንደሚጓዝ ያሳያል ንቁ መሆን አካባቢን መቃኘት ዋጋ እንዳለው ጭምር የሚያሳይ ንቁ ድራማ ግዜ ቢሰጡት የሚያተርፉበት ነው ። 

ሁሉም ያለው አቦል ከመዝናኛ አምድ ባሻገር ሆኖ በቁምነገር የተሞላ የሀገር ገፅታ የሚያሳይ የማህበረሰብ መልክን ደግ የሆነውን የሚያጎላ ከክብር ያነሰው ደሞ በትምህርት መልኩ ማስተካከያ የሚሰጥ የህዝብ ነፀብራቅ ነው በሁሉም ይዘት በድራማ ፣ በሲትኮም ፣ በመዝናኛ ዝግጀቱ ጭምር እነሆ የቤት ጓዳ ደሞ የህይወት ክብደት የኑሮ ጫናን ለመቋቋም ሲባል የሚከፈል መስዋእትነትን ባማሩ ትዕይንቶች የሚተርክ ሌላው የመዝናኛ አማራጭ ነው በአቦል ቲሺ ። 

የቤት ጓዳ የብዙዎች መልክ ፣ የቅርብ ምንአልባት የራሳችን ታሪክ ሊሆን ይችል ይሆናል አጋጣሚ ፣ የመኖር እጣ የዘመን ጅረት የሚወልዳቸው ክስተቶች አቅጣጫ የሚቀይሩ ያልታሰበ መንገድ እና ምርጫ ላይ የሚጥሉን መሆናቸውን የሚያስረዳ እጅግ አስተማሪ ነው የቤት ጓዳ ተከታታይ ድራማ ። 

እድል ለባለ እድለኛው የፀሎት ምላሽ የሰርክ ልመናው ስጦታ ናት ፣ ለከዳችው ደሞ ሁሌም የሚረግማት የቅርብ ጠላቱ ናት የቤት ጓዳም ይህን የብዙዎችን ታሪክ በጥሩ የምስል ቅንብር የድምፅ ጥራት የመቼት ሙላት የሚከሽን ነው ። 

ይህን ሁሉ ያለው አቦል ቲቪ ነው ጎራ ይበሉ አምሮ አድሰው ቁምነገር ይሸምታሉ አቦል ቲቪ ከመዝናኛ ባሻገር በአማራጭ የተሞላ ባለብዙ መልክ በሁሉም የእድሜ እርከን ላይ የሚገኙ ተመልካቾች ምርጫቸው የሚያደርጉት ነው ሁሉም ያለው ነው አቦል ቲቪ ።

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed