channel logo
channel logo

Demakochu

465CompetitionPG13

ደማቆቹ ምዕራፍ 2 በአዲስ መልክ።

ዜና
20 ኤፕሪል 2025
የሚወዷቸውንና የሚያደንቋቸውን ሁሉንም ታዋቂ አርቲስቶች በአንድ ቦታ የሚያገኙበት ደማቆቹ ጌም ሾው።
Demakochu S2

በስራቸው ፣ በህይወት ገፅ የእድሜ ዘመናቸው የፊት የሚባሉትን በደማቆቹ በመጋበዝ የስራ ጅማሬውን ፣ የሚወዱትን በቅድሚያ የሚከውኑትን ብቻ ሁሉንም አንድ በአንድ እያነሳ በጨዋታ እያዋዛ ደመቅ ያለ ቆይታ አሳታፊ በሆነ የማጋፈር ስልት በሀሴት ለምን አለቃ እያስባለ ይዘልቃል ደማቆቹ ። 

ይህ ተመራጭ ባለ ብዙ መልክ መሰናዶ በአዲሱ ምዕራፍ ሁለት በስራቸው እጅ በአፍ ያስጫኑትን የአደይ ፣ የእሳት እራት ፣ የአስኳላ ተከታታይ ድራማ ተሳታፊዎቹን በመጋበዝ አዝናኝ ፣ አስተማሪ ቆይታ ለማድረግ ዝግጀቱን አጠናቆ ወደናተ ለመድረስ ዝግጁ ሆኗል ። 

በምዕራፍ ሁለት ደማቆቹ ይበልጥ ደምቆ በአዲስ እንግዳ በልዩ ሃሳብ ተሞልቶ ወደናተ ይመጣል ። 

የሃሳብ ነፃነት የእንግዶች ከፍታ ፣ ሰውነት የሚታይበት ደማቆቹ በምዕራፍ አንድ የነበረው ክብሩ ሞገስ ደርቦ በምዕራፍ ሁለት ከች ብሎ ከበሮ ላይ አጣጥሙኝ እያለ ነው ይህ አስተማሪ ፣ አዝናኝ መሰናዶ በጉጉት የሚዘልቅ ያለፈውን የማይረሳ መጪውን መሰረት የሚያደርግ የዝነኞች ሜዳ የህይወት አካፋይ አንዱ መልክ ነው ። 

ደማቆቹ መሰናዶ ውስጥ አዋቂ የእንግዶች ባህሪን የተረዳ በዛው ባህሪ ላይ ተንተርሶ አዝናኝ ሳቅ ጨዋታ ጫሪ ጥያቄዎችን በማቅረብ እንግዶችን በማዝናናት የሚወዱትን ቀድሞው የተረዳ በመሆኑ ተመልካች እና እንግዳው ለሰውነት በቀረበው ጥያቄ በእኩል ተዝናኖት በደማቆቹ ይደምቃል መቼም ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል ይሉ የሀገሬ አበው በዚህ አሳታፊ ፣ አሸናፊነት በጋራ መስማማት ማለትም ተሸናፊው አምኖ እና ፈቅዶ እንካ ድሉን በሚልበት መሰናዶ ላይ በአቅራቢው የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች ለእንግዳው ቤተኛ ናቸው እሱም በደስታ ያለ ማፈርና ወደኋላ ማለት ሁሉንም ጥያቄ አዝናኝ በሆነ መልኩ ይመልሳል ማቆቹ በዚህ መልኩ የቤተሰብ ጨዋታ መስሎ ይዘልቃል ። 

ደማቆቹ በአቀራረብ ይዘት የቤተሰብ ውይይት መልክ ገፅ ያለው በመሆኑ ሁሉም እንግዳ በነፃነት የሚጫወትበት ሃሳቡን በምክንያትነት ላይ ተመስርቶ የሚገልፅበት መድረክ ነው ። 

ሁሉም እንግዳ ከአቀማመጥ ጀምሮ የተለያየ ቦታ ላይ አለመሆኑ አቅራቢው ቤተኛ የሆኑ ጥያቄዎችን በመጠየቁ ቤተሰባዊነት ፣ ሰውነት ፣ ፍላጎት እውነተኛ ስሜት በደማቆቹ ይንፀባረቃል ይህም ሌላው ተወዳጅ ተመራጭ የሚያደርገው ጎኑ ነው ። 

ደማቆቹ  ለበጎነት የቀረበ ሰውነትን የሚያከብር መረዳዳትን እንዲሁም ሌሎችን ማሰብ ሰባዊነት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ግዴታ ነው በሚል አሸናፊው አካል ሽልማቱን ለበጎ አድራጎት ያውል በሚል አላማ የእርስ በእርስ አብሮነትን የጋራ እሴትን ለማጎልበት አላማ ያለው በዚህ መልኩ የሚዘልቀው ይህ ዝግጅት የጋራ እሴት ፣ የህብረት አንድነት ዋጋ ለቤተሰብ ለሀገር ያለውን ሚና በአዝናኝ አቀራረብ ያመላክታል ። 

ይህ አሳታፊ መሰናዶ በየ መስካቸው የደመቁትን በሞያ ጭምር ከፍ ያሉትን ጀግኖች በመጋበዝ ሌላውን የህይወት መልክ የሚያሳይ ነው በዚህ ግዜ የመጡበት የህይወት መንገድ ፣ የገጠማቸው ፈተና ያለፉበት ስልት በአዝናኝ ቆይታ ሳቢ ማራኪ በሆነ አቀራረብ አስተማሪ ቁምነገር አዘል ሆኖ ተከሽኖ ይቀርባል የሰው ልጅ እንደዋዛ ከስኬት አይደርስም ብዙ ውጣ ውረድ አለ የሚለውን ለማስረፅ ካማረው ህይወት ጀርባ ልፋት ፣ ፍፁም ትጋት መኖሩን ለመናገር ከፈረሱ አፍ ይሉ ከባለ ህይወቱ የሚማሩበት ነው እንዲሁም ጀማሪዎች የነገ ተስፈኞች የሚማሩበት መንገዳቸውን የሚቀይሱበትና ምርጫቸውን የሚለዩበት ነው ። 

የምዕራፍ ሁለት እንግዶች ለማን ይሆን ሽልማታቸውን የሚሰጡት ምን ጉዳይ ይነሳበታል ፣ እንዴት እዚህ ደረጃ ላይ ደረሱ ምንን አልፈው የሚሉትን በስፋት ደማቆቹ በምዕራፍ ሁለት ይዳስሳል ። 

እነሆ ደማቆቹ በምዕራፍ ሁለት ይበልጥ ደምቆ መልኩን መስሎ በተወዳጁ አቦል ቲቪ ወደናተ ይደርሳል ደማቆቹ 
የደመቁትን በፍካት ያሳያል ።

#ደማቆቹ ምዕራፍ 2 ዘወትር አርብ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed