በማን ቢዝነዝ ማን ይከብራል? በማን ወንጀል ማን ይታሻል? በማን ፍቅር ማን ያሴራል? በማን ሚስጥር ማን ይፀናል? በማን ግዛት ማን ይገዛል?
የግዛት ድራማ ይዘት እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የተፈጠረውን ብጥብጥ እንዴት የቤተሰቡን አባሎች እንደሚቀይር ያስቃኘናል።
የግዛት የመጀመሪያዎቹ 5 ክፍሎች ይሄን ይመስሉ ነበር፡
የቤቱ አባወራ ተፈሪ ባለቤቱ ሀረግን በልጃቸው ሰርግ ዋዜማ ከቤት መውጥ እንዳለባት ይነግራታል። ቤተሰቡ የሀብታቸው ምንጭ የመሳሪያ እንቅስቃሴ ወንጀል መሆኑን እንረዳለን።
በሰርግ ቀን መራራ ሀዘን። የኪያ ደስታ ቀን በአባቷ ግድያ ምክንያት ይጨልማል፣ ማን ነው ተፈሪን የገደለው?
የተፈሪ ገዳይ ይጋለጣል እና ማንነቱ ያልተጠበቀ ነው።
ገዳዩ የተፈሪ ግድያ ዋና መርማሪ ተሾመ ልጅ፣ ሞገስ ነው።
ቤተሰብ ሀረግን ከተፈሪ ቀብር ዝግጅት ሊያስወጣት ይሞክራል ግን በዚህ ሁሉም ሰው አይስማማም።
የሀረግ ወንድም ጎሳዬ ሀዘኗን መተወን እንዳለባት ሀረግ እንድትስማማ ያደርጋታል።
በሌላ በኩል የሀረግ እና ተፈሪ ልጆች የእናት እና አባታቸው ትዳር እንዴት በችግር እንደተሞላ እንደማያውቁ ተረድተናል።
የተፈሪ ግድያ ከሀረግ ጋር እንደሚገናኝ መጠርጠር እንጀምራለን። መርማሪ ተሾመም ሀረግን መጠርጠር ይጀምራል።
የመጀመሪያ 5 ቅፍሎች ልብ አንጠልጣይ ነበሩ። ድራማውን በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡30 ይከታተሉት!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed