channel logo
Gizat S1

የተፈሪ የመጀመሪያ ልጅ ሰመረን ቀረብ ብለን እንመልከተው – ግዛት

ዜና
27 ጁን 2025
ሰመረን የሚገልፀው ቋንቋ እልህኛ እና ስሜታዊ ነው።
who is semere article gizat

ሰመረ የአባቱ እርዳታ ሳይኖረው እንደምንም ብሎ እራሱን ጥሩ ቦታ አድርሷል ነገር ግን የአባትን ቦታ የሚተካ ሰው የለምን እና እልህኛውን የተፈሪ የመጀመሪያ ልጅ ሰመረን ቀረብ ብለን እንመልከተው – ግዛት

ሰመረን የሚገልፀው ቋንቋ እልህኛ እና ስሜታዊ ነው።

ሰመረ የተፈሪ የመጀመሪያ ልጅ እና የሀረግ እንጀራ ልጅ ነው። ተፈሪ ጨካኝ እና ለሀብት እና ስልጣን ትልቅ ቦታ የሚሰጥ ሰው መሆኑን ስናስታውስ፣ የቤተሰቡ ህይወት ላይ የፈጠረውን መጥፎ ተፅዕኖ ማየት አይከብድም። ተፈሪ የሚፈልገውን ነገር በእጁ ለማስገባት ሲል ማንንም ቢጎዳ ደንታ የማይሰጠው ሰው ነው። የተፈሪ የመጀመሪያ ሚስት እና ሰመረ ነበሩ። ይሄን በማወቅ የሰመረን ባህሪ ይበልጥ እንድንረዳ ይረዳናል።

የሰመረ ልጅነት

ወላጆቹ የልጅነት ፍቅረኛሞች በመሆናቸው ጥሩ ቤተሰብ ነበረው። ነገር ግን ይህ ሁሉ በአንድ ምሽት ይቀየራል። ለቤተሰቡ ደህንነት ደንታ ሳይሰጠው ተፈሪ ሀረግን በማፍቀሩ ሚስቱ እና ልጁን ከቤት አባሯል። ይህ ለሰመረ ያልታሰበ በደል ከመሆኑ የተነሳ ለሀረግ ትልቅ ጥላቻ ይፈጥርበታል።

እናቱ ተፈሪ የመጀመሪያ ፍቅሯ ስለነበር ተፈሪን አልጠላችውም ይሄ ሰመረ የቤተሰቡን መበተን ተጠያቂ ተፈሪ ሳይሆን ሀረግ ነች ብሎ ስላሳመነው ለእሷ ያለውን ጥላቻ አምቆ ኖሯል። እናም አባቱ ጋር ደግሞ ተገናኝቶ አብሮት መስራት ሲጀምር ላሳለፈው ህይወት ክፍያው ተፈሪ ሲሞት ግዛቱ የእሱ እንደሚሆን እርግጠኛ ነበር።

[በተጨማሪ ይመልከቱ፡ ሀረግ የዘራችውን አጭዳለች]

ሰመረ የተፈሪን አዲስ ቤተሰብ ከተቀላቀለ በኋላ

ሰመረ ከአባቱ ሁለተኛ ቤተሰብ ጋር መኖር ሲጀምር ባዳ ነበር። ተፈሪ የመጀመሪያ ልጁን ይዞ ወደ ቤት ሲመጣ ቤተሰብ እንዲቀበለው ወይም እንዲንከባከበው አላመቻቸም። ተፈሪ ስለሚጠቅመው ብቻ ነው ሰመረን ማስጠጋት እስከጠቀመው ድረስ የልጆቹ ስሜት ደንታ አይሰጠውም።

ሰመረ እና ኪያ

ኪያ እንደ ልዕልት የምትፈልገው ሁሉ ተሟልቶላት ነው ያደገችው። እናቷን ደግሞ ከምንም በላይ ትወዳታለች ስለዚህ ሰመረን ወደያው ነው የጠላችው። ሰመረ አብሯቸው መኖሩ አባቷ ከሀረግ በፊት ሌላ ሚስት እንደነበረው ያስታውሳታል። እናም ይህ የእናቷን እመቤትነት ይረብሸዋል ብላ ስለምታስብ ልትቀበለው አትፈልግም።

ሰመረ እና አሮን

አሮን በሀብት ውስጥ ቢያድግም ለሰው አሳቢ እና ከወንጀል ጋር ያልተነካካ ኑሮ እንዲኖረው ነው የሚፈልገው። ሰመረን እንደ ታላቅ ወንድሙ ቢያከብረውም፣ የአባታቸው የወንጀል ስራ ውስጥ መሳተፉ ሁሌም ያጣላቸዋል።

ሰመረ እና ሀረግ

ሀረግ ሰመረ የተፈሪን የመጀመሪያ ቤተሰብ ስለሚያስታውሳት እና ከተፈሪ ጋር በመስራት የልጆቿን ድርሻ የሚቀማ ስለሚመስላት ትጠላዋለች። ሰመረም ለእሷ ያለው ጥላቻ ሁሌም እንዳይስማሙ ያደርጋቸዋል።

እነዚህ ፈተናዎች እና ግንኙነቶች የሰመረን ማንነት እና ደካማ ጎን ወስነዋል። የአባቱን ግዛት የእራሱ በማድረግ ብቻ የሚያሸንፍ ስለሚመስለው እሱን እስከሚያሳካ ምንም ከማድረግ ወደኋላ አይልም።

Gizat S1
Gizat S1 Poll 3 article

እርስዎ ማንን ነው የሚደግፉት?

Click here to make your selection
ሰመረ
ሀረግ

ግዛት ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed