channel logo
channel logo

Etse Hiwot

465TelenovelaPG13

አንጋፋ እና ተስፈኞችን ያጣመረ ፣ ዕፀህይወት ድራማ

ዜና
30 ጁን 2025
ዕፀህይወት ድራማ በስራቸው አንቱ የተባሉ በልዩ ልዩ የፊልም ስራዎች የተመሰከረላቸው የጥበብ ሰዎችን አጣምሮ የያዘ ድራማ ነው!
Etsehiwot S1 what we love article

ዕፀህይወት ድራማ በስራቸው አንቱ የተባሉ በልዩ ልዩ የፊልም ስራዎች ፣ የመድረክ ትወና እጅ በአፍ ያስጫኑን መስለው ሳይሆን ሆነው ገፀ ባህሪን ተዋህደው የሚጫወቱ ድንቅ የተባሉ አርቲስቶችን ያሳተፈ ከአንጋፋ እስከ ተስፈኞች የተመሰከረላቸው የጥበብ ሰዎችን አጣምሮ የያዘ ድራማ በመሆኑ ተመራጭ ባለ ፍሬ ድራማ ነው ለዚህም ከምርጫ ሁሉ የፊት ይሆናል።       

  • እውነተኛ የህይወት መልክ የሚታይበት

የምድር ህይወት ባለ ብዙ መልክ የፈተና መድረክ ነው ለጀግኖቹ የሚገብር በድላቸው ላይ ድምቀት የሚፈጥር ለሰነፎችም ደሞ በዛው ልክ ባለ ጉልበት ሆኖ የሚፀና ማሸነፍ እስኪ ችሉ ድረስ የሚፈትናቸው የተሳለ ጉዞ ነው ጀግና አወዳሽ ።          

  • ፍቅር እና መስዋዕትነት ፣

እነሆ ህይወት ፣ ፍቅር ፣ ቤተሰብ የሚወዱትን ሰውን ከፍ ብሎ በህይወት ደምቆ ይታይ ዘንድ የሚከፈል መስዋዕትነት የሚተርክ በጥሩ የታሪክ ፍሰት የተካነ በኪን ይዘት የበለፀጉ መቼቶችን የሚያሳይ በመሆኑ ዕፀህይወትን ምርጫ ማድረግ የህይወት ዘዴ የመኖር ትርጉም ይገባን ዘንድ ምክንያት ሆኖ ከፊት የሚቀመጥ የመዝናኛ ፣ የቁምነገር አምድ ሆኖ ተመራጭ ድራማ ነው ዕፀህይወት በዚህ ድራማ የሰው ልጅ በሰርክ ስራው ሁሌ የሚማር ክስተቱ ተመልሶ ወደፊት ለመጓዝ መካሪ ይሻል ለዚህ ደሞ ታማኝነት ያለው ወዳጅ ያስፈልገዋል በዛሬው ዘመን ደሞ ይህን ፈልጎ ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል በዕፀህይወት ድራማ ደሞ የሰው ልጅ በምክር ሳይሆን በድርጊቱ ይማር ዘንድ ድራማው እድል ይሰጣል አስተማሪ ታሪክ እውነት በምክንያት የሚገለጽ ነውና እና ይህም ድራማ በድንቅ ትዕይንት ባማረ የምስል ጥራት እና ቅንብር ተውቦ ሃሳብን ይዞ በልብ ማንጠልጠል እንዴ አለቀ አስብሎ የሚዘልቅ ድራማ በመሆኑ ዕፀህይወት ተመራጭ ነው ።

  • ክብርና ቤተሰብ ቀዕፀህይወት፣

ዕፀህይወት ድራማ የቤተሰብ ጥቅምን ክብርን ማስጠበቅ አንዱ ለአንዱ ጠቃሚ ሆኖ የሚታይበት መስዋዕትነት ስጋ ለብሶ የሚታይበት መልከ ብዙ ድራማ ነው ፍቅር ደሞ ከፍ ብሎ ዋጋ እንዳለው የሚያሳይ ድራማ ነው ዕፀህይወት ።  

  • ፍቅር የሚኖር እንጂ የሚነገርለት አይደለም ፣

በዚህ ድራማ ፍቅርን በስሜት ለመግለፅ ሆነ በቃላት ለመፃፍ በጣም ከሚያስቸግሩ የዉስጣችን ስሜት ውስጥ አንዱ ነዉ ይህም ድራማ የፍቅርን ሃያልነት የስሜት ጥልቀትና ይተርካል።

በዉስጣችን ያለ ግን ደሞ ለመግለፅ በጣም የሚከብደን ስሜት አልባ ጣዕም ነዉ ለዛም ነዉ የተለያዩ ሰዎች ለፍቅር የተለያየ ትርጉም እና ድምዳሜ ሚሰጡት ዕፀህይወት ድራማ በሌላ መልክ ያሳያል ።

ፍቅር የያንዳንዳችን ስቃይ፡ስብራት፡ደስታና ሃዘን ድምር ዉጤት ነዉ፡፡ፍቅር በጣም ከባድ ስሜት ነዉ የፈለገዉን መግደልም ማበርከክም ይችላል በሱ መድረክ ማንም ጀግና የለም፡ይመለከታል፡ፍርድ ይሰጣል፡ያስቃል ያስለቅሳል ከቶ ሁሉም ነገር የመፈፀም ዓቅም ያለዉ ባለ ስጦታ ነዉ ዕፀህይወት ይህ ውስብስብ ስሜት በድምቀት ያሳያል ።

መኖር ትርጉም ያለው የሚሆነው ሌላው ሰው መኖር ሲጀምር መስጠት እንጂ መቀበል አይደለም ፡ መገኘት እንጂ በማስመሰል ዉስጥ ራስክ እንደ ፃድቅ ማስቀመጥ አይደለም ይህም ድራማ በዚህ ልክ ለሰው ልጅ በወጉ የቀረበ ለማስተማር የተዘጋጀ ድንቅ መምህር ነው ዕፀህይወት ድራማ ።    

  • ለቃለ መኖር ፣ ለፍቅር መታመን ይታይበታል ፣

ዕፀህይወት ድራማ የመተማመን ልክን ነው ፣ የህይወት ትርጉም የገባቸው የሚፋለሙበት መድረክ አስተዋይ የበዛበት ። ተጋድሎ የሞላው መልከ ብዙ ገፅ ፈተና የህይወት ደረጃ አሻሽሎ የሚመነጭቅ እንጂ ጎታች አለመሆኑን የሚታይበት ነው  ለተመልካች መንገድ ጠቋሚ አማራጭ የመመልከት እድል የሚሰጥ በመሆኑ የሚባክን ግዜ እንደሌለ በማወቅ ተመራጭ ነው ዕፀህይወት ድራማ ።  

  • ክትመት እና ገጠሩ የባህር ልዩነት ወይንስ ፣

አብዛኞቹ የአለም ስልጣኔ መሰረታቸው ገጠሩ ነው ፣ ምድረ በዳው ከተማ የሆነው ከጋጣ መሬት ተነስቶ ከትንሽ ስልጣኔ ወደ ደማቅ ሃያል ስልጣኔም የመጣው ስሩን ገጠር በማድረግ ነው ዕፀህይወት ድራማ በሁለት እግር ሆኖ የገጠሩን የዋህነት ለሰው ልጅ ያለውን ክብር የሚያሳይበት ክትመትም ቢሆን በመላቅ በሃሳብ መርቀቅ እንጂ የክፋት ገፅ አለመሆኑን ያሳየበት የሚያሳይበት ነው ዕፀህይወት ድራማ ።

የውስጥ ሰላም ፣ ፍቅር ፣ ደስታ ፣ መተማመን ፣ መስዋዕትነት መልክ ይዘው በየ ረድፉ ተሰልፈው በድንቅ ይዘት ይታዩበታል ዕፀህይወት ድራማ ።

እነሆ አለምን ለመረዳት አሰራሩ ለመረዳት ፣ የሰው ውስብስብ አስተሳሰብን ለመመልከት እድል የሚኖሮት በዕፀህይወት ድራማ ነው የሚባክን ግዜ አይኖርም ።

ዕፀህይወት ዘወትር ከሀሙስ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6