1
ዕፀህይወት በ21 አመት የልደት ቀኗ ወላጅ አባቷ ባጋጠመው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወቱ ያልፋል። ልክ የአባቷን ሞት በተረዳችበት ቅፅበት አባቷ በከተማ ሌላ ቤተሰብና ትዳር እንዳለው አወቀች። ዕፀህይወት የሚገባትን ለማግኘትና የቤተሰቧን ክብር ለማስጠበቅ ከባላንጣዋ ጋር ፍልሚያ በይፋ በመጀመር የህይወት ዋጋ ከሚያስከፍሏት አደጋዎች ጋር በድፍረት እንዴት እንደምትጋፈጥ የሚተርክ ቤተሰባዊ ዘውግ ያለው ድራማ ነው።