የአቦል ቲቪ ምርጦች መካከል እንሞካካር የምግብ አለምን በጥበብ አለም ሰዎች ውስጥ ያሳያል ፣ ፍርቱና ድራማ ደሞ የህይወት መልክን የሚያሳይ ሌላው ገፅ የፍቅርን፣ የገንዘብ ዋጋን የመረዳዳት ልክን መስዋዕትነት ጭምር የሚተርክ በመሆኑ ምርጫዬ ነው ።
የኢትዮጵያ የጥበብ ሰዎች ፣ በስራቸው አንቱ የተባሉ ለመድረክ የገዘፉ በህዝቡ ቦታ ያላቸው ድንቅ የትወና ፣ የሙዚቃ ሁሉም የኪነጥበብ ዘርፍ ፈርጥ ከጥበብ መንገድ ወደ ማዕድ ቤት ጎራ ብለው በእንሞካከር የምግብ ውድድር የምግብ ሞያ የእጅ ውጤት ለመከወን ፈረስ በሚያስጋልበው ማዕድ ቤት ከመድረክ ውጪ ምግብ ማብሰል ላይ እንዴት ናቸው የሚለውን ከራሳቸው የሞያ አጋር ጋር ይሞካከራሉ ።
በዚህ በወዳጅ መካከል በሚደረግ የምግብ ፍልሚያ በሞያ አንቱ የተባሉ ሁሉ የእጅ ሞያቸውን ያሳያሉ ፣ ምግብ የሁሉም የስራ እንቅስቃሴ መሰረት ወሳኝ ነው እንዲሁም ከሞያ ውጪ ምግብ ማብሰል ላይ እንዴት ናቸው የሚለውን ለማየት ጉጉት ስላለኝ እንሞካከርን ማየት ደስ ያሰኘኛል ።
በእንሞካከር የምግብ ውድድር ላይ እውቁ ተዋናይ ጄጄ ካሳ ወደር የለሽ አሸናፊ በመሆን አሁንም አሸናፊ ያጣ ምርጥ ምግብ አብሳይ በሚል እንሞካከርን እየመራው ይገኛል አሸናፊ መጥፋቱ እና የተዋናይ ጄጄ ካሳ ለስድስት ዙር መዝለቅ አስገራሚ በመሆኑ ለማየት ምርጫ ሆነልኝ ።
እንሞካከር በዚህ ፕሮግራም ላይ ሁሉም የሀገሪቱ የጥበብ ሰዎች በሁሉም የምግብ ማብሰል ውድድር ላይ የሚያደርጉት የሞያ ትንቅንቅ ከማዝናናት ባሻገር ነው ።
ወጣቶች የሚመርጡት ቀላል ሃሳብ ያለው እንሞካከር የምግብ ማብሰል ውድድር ላይ ሴት ሳይል ወንድ ተዋናይ ጄጄ ካሳ ማሸነፉ የመጨረሻው ሚስጥር ምን ይሆን የሚለው ጥያቄ መልስ እስኪ ሰጠው እንሞካከር መሰናዶ ምርጫዬ ይሆናል ።
ባለ ብዙ አማራጩ አቦል ቲቪ ከእንሞካካር ውጪ የሁሉንም እድሜ ክልል የሚወክል የህይወት ውጣ ውረድን የሚተርከውን ፍርቱና ድራማ በብዙ አስገራሚ የታሪክ ፍሰት የመቼት እና ግጭት ውጤት ታጅቦ በድንቅ ትወና የታጀበ ድራማ በመሆኑ ልክ እንደ እንሞካከር ምርጫዬ ነው ።
ፍርቱና ድራማ የወንጀል ፣ የፍቅር ታሪክን በሚገርም የትወና ብቃት አጅቦ የወጣቶች የስራ ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች የሚያሳይ የጋህዱ አለም የህይወት ትግል ነፀብራቅ መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።
በእንሞካከር የምግብ ውድድር ላይ ተመራጭ የሆኑ የጥበብ ሰዎችን ከስራ ውጪ ምን አይነት ባህሪ አላቸው የምግብ ምርጫ ሞያቸው ምን ይመስላል የሚለውን ለማየት አጓጊ በመሆኑ እንሞካከር ተመራጭ ነው ።
ፍርቱና ደሞ የሰርክ ኑሮ ፣ የህይወት ትግል ወንጀል ሀገር ፣ ፍቅር ደስታ መከራ ተደራርበው የሚታዩበት በመሆኑ በምግብ በመዝናናት በህይወት ዙሪያ ያሉ እውነታዎችን በቀላሉ ለመቃኘት የሚረዳ በመሆኑ ከመዝናናት በእንሞካከርን ስመርጥ ከትምህርት ደሞ ፍርቱናን ምርጫ አደርጋለሁ ።
ፍርቱና የህይወት መልክን በሌላ ገፅ የሚከሰት ሲሆን ፣ እንሞካከር ደሞ የጥበብ ሰዎችን የሞያ ብቃት የሚያሳይ በመሆኑ ተመራጭ አጓጊ ቆይታ ለማድረግ እመርጣቸዋለው ።