channel logo
channel logo

Etse Hiwot

465TelenovelaPG13

አዲሱ የአቦል ቴሌኖቬላ "ዕፀህይወት" ለእይታ ሊበቃ ነው፤ የመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ ምሩቃን ተሳትፈውበታል!

ዜና
30 ጁን 2025
አቦል ቲቪ ከሬድ ፎክስ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር አዲሱን ኦሪጅናል ቴሌኖቬላ ለተመልካቾቹ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል። አዲሱ ዕፀህይወት ድራማ ከግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዲኤስቲቪ ብቻ የሚተላለፍ ይሆናል።
Etsehiwot S1 article cover

አዲሱ የአቦል ቴሌኖቬላ "ዕፀህይወት" ለእይታ ሊበቃ ነው፤ የመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ ምሩቃን ተሳትፈውበታል!

አቦል ቲቪ ከሬድ ፎክስ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር አዲሱን ኦሪጅናል ቴሌኖቬላ ለተመልካቾቹ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል። አዲሱ ዕፀህይወት ድራማ ከግንቦት 28 ቀን 2017 . ጀምሮ በዲኤስቲቪ ብቻ የሚተላለፍ ይሆናል።

ይህ ተከታታይ ድራማ በተዋጣለት የታሪክ ፍሰት የተዋቀረ ሲሆን በባህላዊ ይዘቶች የተሞሉ ስፍራዎችን በላቀ የፕሮዳክሽን ጥራት አካቶ የማይረሳ የቴሌቪዥን ትዕይንት ለማስመልከት ለደንበኞቹ ቀርቧል።

ዕፀህይወት በልብ አንጠልጣይ የቤተሰብ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከአዲስ አበባ ሽቅርቅር ጎዳናዎች እስከብርቋምናባዊዋ የገጠር ከተማ ድረስ ተመልካቾችን ይዞ እንደሚጓዝ ተገልጿል።

የበርካታ አዳዲስና አንጋፋ ተዋንያን ጥምር ድንቅ ስራ ማሳያ የሆነው ይህ ቴሌኖቬላ በተወዳጅ የአማርኛ ፊልሞች እና ቴያትሮች ላይ አድናቆትን ያተረፈው ደሳለኝ ሃይሉ በዚህ ተከታታይ ድራማ ላይ በድንቅ ትወና ብቅ ብሏል።

በመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ የአንድ ዓመት የፊልም ጥበብ ስኮላርሺፕ በኬንያ የተከታተሉት ምሩቃን መልካሙ ሃይሌ ተፅፎ በስሕነማሪያም አበበ "ላይን ፕሮድዩሰርነት" የተዘጋጀው እፀህይወት ድራማ አዳዲስ ጥበበኞችን ከልዩ እይታቸው ጋር ለኢትዮጵያውያን ይዞ መጥቷል።

ዕፀህይወት 35 በላይ ቋሚ ሠራተኞችን ከመቅጠር ጀምሮ 21 መሪ ተዋናዮችን እንዲሁም 20 በላይ ረዳት ተዋንያን እና ሌሎችም ያሳተፈ ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀው Sony FX6 ካሜራ ቀረፃው ተከናውኗል።

ይህ አዲስ ቴሌኖቬላ ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ በአቦል/ዲኤስቲቪ የሚተላለፍ ሲሆን ተመልካቾች ከግንቦት 28 ጀምሮ ዘወትር ሀሙስ እና አርብ ምሽት 2:00 እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል።

ዕፀህይወት ዘወትር ከሀሙስ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6