የቤተሰብ ታሪክ በልጆች ፍላጎት ይቀጥላል ወይ ልጆችስ ለዚህ ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ በምን መልኩ ይተጉ ይሆን ሆይ የሚለውን ውስብስብ የተጋድሎ ምዕራፍን የሚተርክ ወዳጅ ፣ ዘመድ ቤተሰብ በህይወት ውስጥ ምን ያህል ወሳኝ መሆናቸውን በግልፅ የሚያሳይ በሚገርም የምስል ቅንብር የተዋበ ድራማ ነው ዕፀህይወት ድራማ ።
በዚህ አስገራሚ ድራማ ነገሮች በፍጥነት እየተቀየሩ ነው ዕፀህይወት የአባቷ ንብረት ወራሽ ለመሆን የሚያበቃትን የኑዛዜ ደብዳቤ በቀጣይ የድራማው ትንቅንቅ ልታገኘው ትችል ይሆን ዕፀህይወት በቀጣይ መልሰ አለው ፣ ለወትሮው የምድር ህይወት ባለ ብዙ መልክ ነው የቅርብ ያሉት የሩቅ ሲሆን መመልከት ፣ የሩቅ ዋጋ አልቦ ሰዎች ደሞ ባልተገመተ ሰአት እና አጋጣሚ ደራሻ ባለውለታ ሲሆኑ ማየት የምድር ጉራማይሌ ገፅታን በመልክ ያሳያል ዕፀህይወት የሃብት ተካፋይ መሆን የለባትም በሚል ሌላ ተቀናቃኝ በግራ በኩል ብቅ ብላለች ሰብለ ከባሏ ፍቃዱ ሞት በኋላ የድርጅቱ ወራሽ መሆኗን ለቦርድ አባላት ብታሳውቅ እውነት አሸናፊ ነው እና ጠበቃ ሰውነት ዕፀህይወት የድርጅቱ ግማሽ ሀብት ወራሽ መሆኗን ያስረዳል ።
ሰብለን የሃብት ማማ ላይ የሚሰቀለው አጋጣሚ በጠበቃ ሰውነት ከሽፏል ምን ይሆን የዕፅህይወት ቀጣይ ፈተና ድርጅቱን ከመምራት እስከ ታሪክ ማስቀጠል ያለው ከባድ ጉዞ በምን ይታለፋል እንዲሁም የሰብለ እልህ የተሞላበት የተሸነፍኩ ስሜት በምን ባህሪ የበቀል እርምጃ ይጓዝ ይሆን ድራማው በቀጣይ ክፍለ መልሰ አለው ።
ግን አሁንም አንድአንድ ምልክቶች እየታዩ ይገኛሉ አሸናፊ ሰብለን ለማስደሰት ዕፀህይወትን ፣ ፍቃዱ አባቷ አለመሆኑን በፊርማዋ እንድታረጋግጥ በስውር ተልዕኮ በረቀቀ መንገድ ከሃብት ለማስነሳት አባቷን ትክድ ዘንድ
ያደርጋታል የሰብለ ሌላው የእልህ መንገድ መሆኑ ነው ።
በዚህ እውነተኛ የህይወት ሌላውን መልክ በሚተርከው ድንቅ ድራማ እንዴት ለምን ፣ የሚያስብለው እስክንድር ገፅ ባህሪ የነ ዕፀህይወትን ቤት በእሳት ያወድማል ይህም የነ ሰብለ ሌላው እቅድ መሆኑ ነው ፥ ማስገረም ልማዱ የሆነው ዕፀህይወት ድራማ ህይወት ፈተናው ብዙ ጉዞው አድክም ፣ ውል አልባ ይሆናል በዚህ ግዜ እንዴት ፈተናን ማለፍ እንደምንችል ያሳያል ዕፀህይወት ድራማ በሁሉም ክፍል ።
የዕፀህይወት ፈተና ፈርጀ ብዙ ነው የሚታለፍ የማይመስል አስገራሚ እንዴት የሚያስብል ታድያ እነ ዕፀህይወት ይህን የውስጥ መከዳት የሃብት ሽሚያ እንዴት ትለፍ የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው ወገብን ሸብ በማድረግ በፅናት በመቆም የጀርባ ሴራን በመረዳት በብልጠት በሃሳብ ክህሎት ማለፍ አማራጭ የሌለው ውሳኔ ነው ።
በምድር ሲኖር እልፍ አስቸጋሪ የስኬት ፣ ሁለንተና መኖር ላይ ችግሮች አሉ መፅናናት እና መፅናት ደሞ የዚህ ችግር የመፍትሔ መንገድ ናቸው እነ ዕፀህይወት ደሞ የባህሪ ግብር ያላቸው እውነተኛ ሰው ሲሆኑ እውነትን የያዘው ደሞ አሸናፊ ይሆናል ።
ዕፀህይወት ያጋጠማት ፈተና በእውነቱ ከባድ ነው ግን ትወጣ ይሆን ግዜ ደጉ ድራማው መልስ አለው ።
ፍቅር ፣ እምነት ፣ ክህደት ፣ እውነት ፣ ቤተሰብ ፣ ሃብት ፣ በአንድ የህይወት ሜዳው ላይ በግልጽ እና በጀርባ እንደ ባህሪያቸው ገጥመው ከባድ ፍልሚያ ውስጥ ናቸው በዕፀህይወት ድራማ ማን ከማን በቅድመ ተከተል ተፋልሞ ተሸነፈ ፣ አሸነፈ ለሚለው ድራማው መልስ አለው ።
ዕፀህይወት ተከታታይ ድራማ ፥ የህይወት ሌላው መልክ ይገለጥበታል የሰው ልጅ የህሊናው ጥግ ይታይበታል መልኩም ብዙ ባህሪው ልዩ ነውና ።
ዕፀህይወት ዘወትር ከሀሙስ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6