የግዛት ገጸ ባህሪዎች ሁሌም ልብ አንጠልጣይ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። እኛም በተመልካች ተወዳጅ የሆነውን ገጸ ባህሪ ሰመረን አስተሳሰብ ይበልጥ ለመረዳት እና ስሜት የሚቀሰቅስ ታሪኩን የሚተውነውን ታምራት በለጠ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገናል!
ይበልጥ ስለ ተዋናይ ታምራት በለጠ እና ሰመረ ለማወቅ ማንበብ ይቀጥሉ፡
ቃለ መጠይቅ
1. ጤና ይስጥልኝ፣ እራስዎን እና በአቦል ቲቪ ላይ የሚጫወቱትን ገጸ-ባህሪ አስተዋውቁ።
ስሜ ታምራት በለጠ ይባላል። በ አቦል ቲቪ ግዛት በሚለው ድራማ የሰመረን ካራክተር ነው የምጫወተው።
2. ወደ ቀረሳ ከመውጣትህ በፊት የምትወደው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴህ ምንድን ነው?
ከቀረፃ ሰአት በፊት ረጅም ሰአት ቤት ስለማሳልፍ አንዳንድ መፅሀፍቶችን እና ለካሬክተሬ የምረዳኝ የትወና ክህሎቶች አያለው አዳብራለሁ። በተጨማሪም ስፖርት አዘወትራለው። ቡና ስለምወድ የተረጋጋ የቡና ሰአት አሳልፋለሁ።
3. የሴሜሬን ባሕርይ በሦስት ቃላት ግለጽ።
ግልፍተኛ፣ ቤተሰቡን የሚወድ፣ ጠንካራ ሰራተኛ።
4. የሰመረ አስተዳደግ ባህሪው ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ፈጥሯል?
ሰመረ በልጅነቱ ማየት የሌለበትን ፈተና የተጋፈጠ ልጅ ነበር። አባቱ በጨረማ ከእናቱ ጋር ያባረረው ከርታታም ነበረ። እራሱ እና እናቱን ከችግር ለማውጣት ሲል ብዙ የስቃይ ግዜአትን ያሳለፈ ልጅ ነበር። የወንበዴነትን ህይወትን በጠዋት በግዴታ የተቀላቀለ ልጅ ነው።
5. የሰመረ ባህሪ ከአንተ ጋር ምን ያህል ይመሳሰላል?
ሰመረ ከታምራት ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር ጠንካራ ሰራተኝነታቸው እና ለቤተሰቡ ያለው አስተሳሰብ ብቻ ነው። ሰመረ በብዙ መከራ እና ፈተና ውስጥ ያለፈ ስለሆነ ስሜታዊነት ግልፍተኝነት ያጠቃዋል። ማግኘት የሚፈልገው ህይወት ሳያገኝ ስለሆነ የሚኖረው እልኸኝነት እና ጉልበተኛነቱ እራሱን መግዛት እስከሚያቅተው ድረስ ይቆጣጠሩታል። በዚህ በርካታ አስከፊ ውሳኔዎችን ወስኗል።
6. ሰመረ አባቱን [ተፈሪን] ይወድ ነበር? ወይስ ሥልጣኑን ይፈልግ ነበር?
ሰመረ በዚህ ዙሪያ ሁለት አይነት ስሜት ነው ያስተናገደው። የመጀአሪያ ተፈሪ በህይወት በነበረበት ግዜ በአባቱ አይን ሙሉ ሆኖ መታየት በአባቱ መደነቅ ለአባቱ ኩራት ሆኖ መኖር ነበር የሚፈልገው።አባቱንም ይወደው ነበር። የቀን ጎዶሎ አባቱን ሲያሳጣው ግን ስሜቱ ተቀየረ። ይህም የአባቱን ግዛት ሀይህ ቦታ መቆጣጠር ነበር የሚፈልገው።
7. ሰመረ የራሱ ታሪክ ጀግና ነው ብሎ ያምናል ብለህ ታስባለህ?
አዎ የሚነግስ ይመስለኛል። ምክንያቱም ግዛቱን ለመቆጣጠር (Hero) ለአሆን የማያበቃ ተጠያቂነት የለበትም።
8. ተፈሪ ዛሬ በሕይወት ቢኖር ኖሮ ሰመረ ምን ይለው ነበር?
ተፈሪን በህይወት ቢኖር ይሄንን ሁሉ ደስተኛ ሆነህ እንዴት መያዝ ቻልክበት እለው ነበር።
9. የአንተ ገጸ-ባህሪ ታሪክ በዛሬው የዜና ዜና ላይ ቢጠቀስ ኖሮ ምን ይወራለት ነበር?
ኩራት ነው የሚሰማኝ። ሰመረ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን እና ተወዳጅነትን ያገኘ ካራክተር ነው። ማንም ወንድ መሆን የሚፈልገው አይነት ወንድ ስለሆነ ብዙዎች ወደውታል።እኔም ሰመረን ከሚወዱት ውስጥ ነኝ።
10. ተዋናይ ባትሆን ኖሮ ምን ትሰራ ነበር?
እራሴን በይዙ የፕሮዳክሽን ክፍል ውስጥ ስላሳለፍኩ ከ አርት ውጪ አስቤው አላውቅም። ግን መመለስ ካለብኝ አክተር ባልሆን ነጋዴ የምሆን ይመስለኛል።
ለጥያቄዎቹ አመሰግናለሁ።
ይህ ቃለ መጠይቅ ስለ ሰመረ ገጸ ባህሪ እና ታሪክ ለማወቅ እረድቷችኋል?
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ኮሜንት በማድረግ ሀሳባችሁን ያሳውቁን!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6