channel logo
Gizat S1

ሀረግ vs ሰመረ፡ በማን ግዛት ማን ይገዛል?

ዜና
31 ሜይ 2025
በወንጀል የተገነባውን ግዛት ማን ይመራዋል።
Gizat S1 hareg vs semere

ከተፈሪ ሞት በኋላ የቤተሰቡ ዋና የገንዘብ ምንጭ መጨረሻው አላማረም ነበር። የተፈሪ ቤተሰብ በህገ ወጥ የተገነባውን ቢዝነስ የሚመራ ሰው በአስቸኳይ ያስፈልገው ነበር። ሰመረ ቀጣዩ መሪ እንደሚሆን ምንም ጥርጣሬ አልነበረም ነገር ግን ሰመረ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ያለውን ግንኙነት ማበላሸት ሲጀምር፣ ሀረግ የቤተሰቧን ደህንነት ለመጠበቅ ስትል ቢዝነሱን ለማስተዳደር ትወስናለች።

የሁለቱ ጥሩ እና መጥፎ ባህሪ እና ችሎታ ይሄን ይመስላል፤

ሰመረ

ጠቃሚ ባህሪዎቹ፡

  • የተፈሪ የመጀመሪያ ልጅ።
  • ስለ ቢዝነሱን ከተፈሪ ጋር በመስራት ሲማር ቆይቷል።
  • ስኬታማ ህገ ወጥ ቢዝነስ ለማስተዳዳር የሚያስፈልገው ጭካኔ አለው።
  • የተፈሪ ወንድም ምትኩ ድገፋ አለው።

ጎጂ ባህሪዎቹ፡

  • በጣም ስሜታዊ።
  • በዘዴ የሚያስፈልገውን ከቢዝነስ ባልደረቦችን መውሰድ አይችልም።
  • ለሴት ልጅ ክብር የለውም።
  • ሁሉም ሰው እንደ በታቹ የሚቆጥረው ስለሚመስለው ቀድሞ ይሳደባል።

 

ሀረግ

ጠቃሚ ባህሪዎቿ፡

  • የተፈሪ ልጆች እናት እና ሚስት።
  • ለልጆቿ ብላ ምንም ከማድረግ ወደኋላ ስለማትል የሚያስቆማት ሀሳብ የለም።
  • ከተፈሪ ጋር ስብሰባ ለይ ስትሳተፍ በመኖሯ የቢዝነሱ ባልደረቦቻቸውን ልምድ እና ባህሪ ጠንቅቃ ታውቃለች።
  • ወንድሟ ጎሳዬ በሁሉም ነገር ይደግፋታል።

ጎጂ ባህሪዎቹ፡

  • ተፈሪን አስገድላዋለች እና ልጆቿ ካወቁ ይጠሏታል።
  • የአሮንን ተቃውሞ አለመስማቷ ግንኙነታቸውን እየቀየረው መጥቷል።
  • የተፈሪ ገዳይ እና መርማሪ ተሾመን ልጅ አስገድላዋለች።

የሰመረ እና ሀረግን ደካማ ጎን እና ባህሪ ዘርዝረናል።

እርስዎ ለማን ነው የሚደግፉት?

ሀረግ

ሰመረ

ግዛት ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed